በጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 1 /አንድ/ አውቶቢስ፣ 1 /አንድ/ ዶልፊን እና 1 የውሃ ቦቲ ተሸከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ (01) ዓመት የሚቆይ ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር:- CC-MBO/CNB/02/2018/2025
በጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 1 /አንድ/ አውቶቢስ፣ 1 /አንድ/ ዶልፊን እና 1 የውሃ ቦቲ ተሸከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ (01) ዓመት የሚቆይ ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል።
በሰንጠረዡ በተቀመጡ ሃሳብ መሰረት አሸናፊ ከሚሆን ድርጅት ጋር ውል መዋዋል ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የተሽከርካሪ አይነት |
ሰው የመጫን አቅም |
የስሪት ዘመን |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1. |
አውቶቢስ |
60 እና ከዛ በላይ |
2010 እና ከዛ በላይ |
1 |
|
|
2. |
ዶልፊን /ሚኒባስ/ |
14 እና ከዛ በላይ |
2010 እና ከዛ በላይ |
1 |
|
|
3. |
የውሃ ቦቲ |
ባለ 22,000 ሊትሪ የሚይዝ |
2010 እና ከዛ በላይ |
1 |
ስለሆነም ተሽከርካሪዎችን የሚያመለከተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታው ሠነዱ ላይ
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት
1 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለአውቶቢስ፤ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለዶልፊን /ሚኒባስ/ እና ለውሃ ቦቲ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንከ የተመሰከረለት CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሠነዱ ጋር እያይዘው ማቅረብ
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሞያሌ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ከጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ ለ10 ቀን በአየር ላይ የሚቆይ መሆኑ ይታወቅ።
8. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CPO በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ለአንድ ዓመት ውል ይፈራረማል።
10. ጨረታውን የምናስተናግደው በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ (car by car) ይሆናል፡፡
11. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም ካለውም ፓራፍ መደረግ አለበት።
12. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸው ማህተም እንዲሁም ስም፣ አድራሻ፣ ስልከ፣ ኢሜይል አድራሻ ማድረግ አለባችሁ።
13. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው መኪናዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
14. ተጫራቾች ተመሣሣይ የሰርቪስ ዋጋ ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በእጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን።
15. ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የጨረታ ሰነድ መሸጫና ጨረታ መክፈቻ ቦታ ሞያሌ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን አስተባባሪ 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር:-046-4-44-09-52/046-4-44-12-18/09-26-42-39-50
ደውለው ይጠይቁ::
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሴ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
