የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀት አመት ለአቃብያነ ህግ የፕሮቶኮል ልብስ እና ለኮሚኒኬሽን ዳይሬከቶሬት ለስራ አገልግሎት የሚውል የካሜራ እቃዎች በድጋሚ በወጣው ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
በድጋሚ የወጣ ግልጹ
የጨረታ ቁጥር፡ ፍቢ 002/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀት አመት ለአቃብያነ ህግ የፕሮቶኮል ልብስ እና ለኮሚኒኬሽን ዳይሬከቶሬት ለስራ አገልግሎት የሚውል የካሜራ እቃዎች በድጋሚ በወጣው ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት 1 |
የሚፈለገው ልብስ |
ሎት 2 |
የሚፈለገው እቃ |
|
1 |
የወንድ አቃብያነ ህግ |
4 |
ካሜራ |
|
1.1 |
ኮትና ሱሪ ሙሉ ልብስ ሱፍ መጠኑ 80% |
4.1 |
የካሜራ ሄድ |
|
1.2 |
ሸሚዝ |
4.3 |
ዜብራ ሌንስ |
|
1.3 |
ከረቫት |
4.4 |
ሀርድ ዲስክ |
|
1.4 |
ጫማ |
4.5 |
ኒክ ማይክ |
|
2 |
ለሴት ኢቃበያነ ህግ |
4.6 |
ፓውዛ መብራት |
|
2.1 |
ሸሚዝ |
4.7 |
ሚሞሪ መገልበጫ |
|
2.2 |
ከረቫት |
5 |
አስፒከር ሞንተርቦ (ዋየር ለስ) |
|
2.3 |
ጫማ |
6 |
ዋይርለስ ማይክ ከነ እስፒከሩ |
|
2.4 |
ኮት እና ሱሪ ወይም ኮት እና ጉርድ ቀሚስ |
|
|
|
3 |
የተለያዩ መጠን ያላቸው የኢትዮጵያ ሰንደቅ |
|
|
ለመወዳዳር የሚያስፈልጉ፡-
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በመንግስት ግዥ በጨረታ እንዳይሳተፍ ታግደው የነበረ ከሆነ እገዳው የተነሳላቸው ስለ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሰነድ ማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ /10/ ስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለሚወዳደሩባቸው ልብሶች ጥራቱን የጠበቀ ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ለሚጫሩቱበት የአቃብያነ ህግ ፕሮቶኮል ልብስ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ለካሜራ እቃዎች ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ስም ሲፒኦ ማስያዝ ግዴታ ነው፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት፣ በማህተም በማረጋገጥ እና በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የቴክኒካል ሰነድና ፋይናንሻል ሰነድ በማለት ለይተው ማቅረብ ሲኖርባቸው ይህንኑ መረጃ ከገዙት ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው አቅርቦት መጠን 25% በላይ መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማሰታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በማስገባት በ11ኛው ቀን 3፡00 (ሶስት ሰዓት) ተዘግቶ 3፡30 (ሶስት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እለት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ ሜክሲኮ ሰነዱ የሚሸጠው ፊሊፕስ ህንፃ አጠገብ ፍትህ ቢሮ ህንፃ ከፌዴራል ፖሊስ ወረድ ብሎ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ህንፃ 4ኛ ወለል ላይ ይሆናል፡፡
ስልክ 011-51-59-54
የአዲስ አበባ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
