Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa University College of Agriculture (ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462204740
  • Website
  • Deadline21 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid Security10,000.00
  • opening date2025-10-21 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ለረዥም ጊዜያት ተከማችቶ የቆዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Hawassa University College of Agriculture (ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ)


የቁርጥራጭ ቆርቆሮ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር HUCA/NCB/steelsale/2018/BY

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ለረዥም ጊዜያት ተከማችቶ የቆዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 250/ሁለት መቶ ሀምሳ ብር በባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000013552464 ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ የውስጥ ገቢ በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ለሚፈልጉት የንግድ ዘርፍ የዘመኑ እድሳት የተከናወነበት በዘርፋ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡብትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ለአጠቃላይ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ግምት ዋጋ ሲፒኦ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ / 10,000.00/ አስር ሺህ ብር በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ ስም ለሚወዳደሩበት ጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ከፍለው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ደረሰኙን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን_ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5. ጨረታው ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ግቢ በሚገኘው ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ቁርጥራጭ ቆርቆሮ የአንዱን ኪሎ ግራም ዋጋ በመጥቀስ በጨረታ ሰነዱ መሙላትና አጠቃላይ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መከፈል የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

7. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0462204740 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለሚከናወነው የግንባታ ሥራ በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በብሔራ...

READ MORE