የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለመፈጸም አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
Dire Dawa Administration Education Bureau (የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለመፈጸም አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. የምግብ ሸቀጣሸቀጥ ግዥ
ስለዚህም፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ለ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር መክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢነት ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- ታክስና ክሊራንስ የ2018 ዓ.ም ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 22 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በድሬዳዋ እስታዲዮም ጀርባ በአዲስ ህይወት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው የድሬዳዋ መምህራን ኮሌጅ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ጊዚያዊ ቢሮ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሪት ቢሮ በመቅረብ መግዛት የሚችል፣
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋቸው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዛው እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ይህ ቀን ግን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ቢሮው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 02511128435 መደወል ይችላሉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት
