Tender Detail

Tender Details

  • Company Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ወርቁ ሰፈር (ውሃ ልማት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መስጊዱ እካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 17 51 51
  • Websitehttps://www.dce-et.com/
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


 

የጨረታ ቁጥር DCE/ ST/147/2025

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

የዕቃው አይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች

ለዋና መስሪያ ቤት

DCE/ST/147/2025

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት

20,000.00

 

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡብት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅረቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-mail & Info@dce-et.com

የድረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

ፖስታ ቁጥር 3414

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender