Tender Detail

Tender Details

  • Company ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0114 42 25 44
  • Website
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Vehicle

ድርጅታችን ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አንድ ቶዮታ ፒካፕ እና ያሪስ ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አንድ ቶዮታ ፒካፕ እና ያሪስ ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ቀጥሎ በተጠቀሰው መስፈርት መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ከኢትዮጵያ ባሌስትራ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት በመገኘት ተሽከርካሪው ባለበት በአካል ማየት የሚችሉ ሲሆን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

2. የጨረታውን ሰነድ ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ላይ መሳተፍ አይችልም።

3. ተጫራቹ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ተሽከርካሪውን በማየት ዋጋ መስጠት ይችላሉ።

4. አንድ ተጫራች ሌላ ተወዳዳሪ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል።

6. ተጫራቾች ያስያዘው ሲፒኦ ለተሸናፊዎች ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ማግስት ጀምሮ የሚመለስላቸው ሲሆን ለአሸናፊው ግን ባሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ ይሆናል።

7. የጨረታው ፖስታ ሲከፈት መስፈርቶቹን አሟልተው ያልቀረቡ ተጫራቾች ውድቅ ይደረጋሉ፡፡

8. የጨረታው አሸናፊ የሚጠበቅበትን ክፍያ ፈጽሞ በ10 ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል። ካልሆነም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረግና ጨረታው ይሰረዛል።

9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት አስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተከፍቶ ውጤቱ ለተሳታፊዎቹ ግልጽ ይደረጋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራች የስም ማዛወሪያ ቴምብር እና አስፈላጊውንም የመንግሥት ክፍያዎችን ይከፍላል።

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 42 25 44/0966-02 00 68 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender