Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ልማት ማህበር
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0926277854
  • Website
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10%
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Vehicle

የሲዳማ ልማት ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ልማት ማህበር


ያገለገሉ ተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ልማት ማህበር ዋና መ/ቤት የጨረታ ቁጥር -ዐ01/2018

 

የሲዳማ ልማት ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች የሚገኙበት ቦታ በሲዳማ ልማት ማህበር ሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ ፓርክ እና መዝናኛ ማዕከል (አሞራ ገደል) ግቢ ውስጥ ሲሆን

  1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በአካል በመገኘት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ አስቀድሞ ማየት እና ከተመለከቱ በኋላ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከ5 የሥራ ቀናት በፊት በአካል በመቅረብ ሲዳማ ልማት ማህበሩ ዋናው መ/ቤት ማሳወቅ አለባቸው። ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራቾች ጨረታው ከታሸገ በኋላ ለሚያቀርቡት አቤቱታ ተቋሙ ምንም ምላሽ ለመስጠት አይገደድም፡፡
  2. በጨረታው ማንኛውም ግለሰብ /ድርጅት/የሆነ መሳተፍ ይችላል።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጣ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ኦርጅናል እና ኮፒውን ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል።
  4. በውክልና ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ እና የወካዩን መታወቂያ ይዞ በአካል መቅረብ አለበት።
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ የሚገዙበትን የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በሲዳማ ልማት ማህበር ስም በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለልማት ማህበሩ ገቢ ይሆናል።
  7. የአሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሠሌዳ እንደተገለጸ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች ወዲያውኑ CPO ተመላሽ ይደረጋል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያውን ለመረከብ ሲመጣ በቅድሚያ የCPO ኮፒ፣ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ፣ ተወካይ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች በአንድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ከአንድ ጨረታ በላይ መጫረት አይችሉም፡፡
  10. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ተሽከርካሪዎችን የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 300 ብር ወደ ሲዳማ ልማት ማህበር ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013477055 ገቢ በማድረግ በሲዳማ ልማት ማህበር ፋይናንስ እና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  11. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልፅ በአሃዝና በፊደል በመፃፍ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በቀረበው ዋጋ መሙያ ላይ ለሚገዛው ተሽከርካሪ ፊት ለፊት ዋጋውን በመሙላት በፊርማ ማረጋገጥ አለበት፡፡ በፊደል የተጻፈው ለማንበብ የሚያዳግት ከሆነ በአኃዝ የተጻፈው የሚገዛን ይሆናል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በሲዳማ ልማት ማህበር ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአካል ቀርበው መግዛት ይኖርባቸዋል።
  13. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ ለደረሰ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት የለውም።
  14. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
  15. የጨረታ መከፈቻ ቀን በዓል ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  16. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ሙሉ ክፍያውን በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት አለባቸው።
  17. በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት CPO ለልማት ማህበሩ ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ ላይ ይውላል።
  18. ተቋሙ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሠሌዳ በግልጽ ያሳውቃል።
  19. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ የሚመለከት ማንኛውንም ወጭ በራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል።
  20. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 26 27 78 54 / 09 67 74 48 85 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።

 

የሲዳማ ልማት ማህበር ዋና መ/ቤት (ሀዋሳ)

Save Tender