Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ
  • Address በቀድሞ ስሙ የካ ክ/ከተማ አቧሬ ጤና ጣቢያ ተብሎ የሚጠራው በአሁኑ በአራዳ ከ/ከተማ እዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118688278
  • Website
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Furniture , Stationery Materials , Office Equipment

የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ


የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-አ/ጤ/ጣ -001/2018

የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ጨረታ የሚያስፈልጉትን በዋናነት የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ቋሚ የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን (ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ) እና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጥገና ሥራዎችን በምድብ (በሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣ የደምብ ልብሶችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን ፣ ቋሚ እቃዎችን ፣ ህትመቶችን እና ሌሎች የሥራ መገልገያ መሳሪያዎችን እና ሥራዎችን በጥራት ለማቅረብ ወይም ለመሥራት የሚያስችል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው::

2. ተጫራቶች በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በግልጽ የሚታይ የምስከር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋርአያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው መልቀቂያ (ክሊራንስ) እና ሌሎች አስፈላጊ ዶከመንቶችን ኮፒ እያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በምድብ (በሎት) ስለሆነ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሲፒኦ ሰነድ በየምድቡ ሲሆን ለእያንዳንዱ ምድብ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሳሪያዎች /አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ለፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ፣ ለህትመት ስራዎች ለእያንዳንዱ /ብር 5,000.00/ እምስት ሺህ ብር ብቻ) ፡ ለቋሚ ዕቃዎች (ለፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒከስ ) /ብር 8.000.00/ ስምንት ሺህ ብር/ ለልዩ ልዩ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና / ብር 4.000.00 /አራት ሺህ ብር ብቻ/በአራዳ ክፍለ ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (ሲፒአ) ብቻ ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋርበፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት የቴከኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን አሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የሲፒኦ ሰነድ በአሪጅናል ሰነድ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

7. ጨረታው ይህ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጫረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል።

 

8. ጥቃቅን እና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ እና በራሳቸው በሚያመርቱት ዕቃዎች ላይ ብቻ ካደራጃቸው ተቋም ለመስ/ቤታችን የዋስትና ደብዳቤ ከሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቶች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

10. ተጫራቶች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም።

11. ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ሳይሰርዙ፣ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው አገልግሎት ወይም ዕቃ ዋጋውን ብቻ በዋጋ መሙያው ላይ መሙላት አለባቸው፤ ይህን ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውድድሩ ይሰረዛል።

12. ተጫራቶች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት /NAT/ ማካተት አለባቸው።

13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደርያ ዋጋ ሞልተው በታሸነ ፖስታ ውስጥ አድርግው ማቅረብ አለባቸው።

14. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞላው ነጠላ ዋጋ ነው።

15. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በቀድሞ ስሙ የካ ክ/ከተማ አቧሬ ጤና ጣቢያ ተበሎ የሚጠራው በአሁኑ በአራዳ ከ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118688278 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአረዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ

Save Tender