በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ያሎትን እቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመጀመሪያ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2018
በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ያሎትን እቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የደንብ ልብስ cpo,ብር(6,000)
ሎት 2. የጽዳት እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 4. የኤሌክትሪክ እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች cpo ብር (8,000)
ሎት 6. የመኪና እቃዎች cpo ብር (5,000)
ሎት 7. ቋሚ የቢሮ እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት8 የጥገና እቃዎች(ቁልፎችና የመሳሰሉት) cpo ብር (5,000)
ሎት 9 የአጠባ ማሽን cpo ብር (10,000)
ሎት 10. የደንብ ልብስ ስፌት cpo ብር (8,000)
ሎት 11. ሕትመቶች cpo ብር (8,000)
ሎት 12. የመድሃኒቶች cpo ብር (8,000)
ሎት 13. ቋሚ የህከምና መሳሪያዎች cpo ብር (9,000)
ሎት14.የላብራቶሪ ሪኤጄንቶች cpo ብር (5,000)
ሎት 15 ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች (4,000)
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጨራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ሀጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ግብር የመክፈል ግዴታውን የተወጣ መሆኑን የሚገልፅ ከግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. ጨረታውን ሚወዳደሩበት በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ መሆን አለበት።
4. ማንኛውም ተጨራች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በዝርዝር በተገለጸው መሰረት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሲያስገባ (cpo) ብቻ በጤና ጣቢያው ስም አሰርቶ ማስያዝ ይኖርበታል።
5. የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለተሸነፉ ድርጅቶች ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
6. ጨረታውን ለአሸነፉ ድርጅቶች ደግሞ የጨረታው ውል ማስከበሪያ ብር 10% አስይዘው እንደተፈራረሙ በጨረታ ማስያዣ የተያዘው ብር ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ነገር ግን ለአሸነፊ ድርጅቶች ውል ፈርመው በወቅቱ እቃዎቹን የማያቀርቡ ከሆነ ካስያዙት 10% ላይ1% በየቀኑ የቅጣት ይቀነስባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ መግዥ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር የስራ) ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ኮተቤ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 55 ግዥ ክፍል በአካል ቀርበው የጨረታውን ሰነድ እያንዳንዱ በማይመለስ ብር200(ሁለት መቶ ብር)መግዛት ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪ የሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መሰረት በማድረግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙለት አንድ ኮፒ እና ኦሪጅናል በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ከፍል ቢሮ ቁጥር 54 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጓ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት (ሶስት ሰዓት ተኩል) ላይ ይከፈታል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጤና ጣቢያው የሚገዛቸውን እቃዎች 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው፡፡
13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 (ስልሳ ቀናቶች) እና ለተጨማሪ ቀን 28 (ሃያ ስምንት) ቀናት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-05-20-54 ወይም 09-21-83-05-96
ደውለው ይጠይቁ።
አድራሻ፦ ኮተቤ ጤና ጣቢያ 02 ወደታች በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ
