የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደቡብ ቅ/ጽ/ቤት 001/2018
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል
|
ሎት |
የእቃው/ የአገልግሎቱ አይነት |
ማብራሪያ |
|
ሎት 1 |
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት |
|
|
ሎት 2 |
የጽ/ቤቱ የሙሉ ቀን ስራ ትራንስፖርት አገልግሎት |
|
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህም መሰረት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ የታደስ ሊብሬ እና የሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና/ኢንሹራንስ ማሟላት እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሎት 1 5000 (አምስት ሺህ ብር) ለሎት 2 5000 (አምስት ሺህ ብር) በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋርማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1, የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሲሆን ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ለተከታታይ 10(አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ ከከፍያና ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ከፍል ይከፈታል፡፡
4. ተጫራቾች ጨረታው (ቴከኒካል ሰነድ) በሚከፈትበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 አስከ 6፡00 ሰዓት ተሸካርካሪዎቹን ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ የቴክኒከ ፍተሻ ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን በቴከኒካል ያላለፈ ተሽከርካሪ ለዋጋ ውድድር አይቀርብም፡፡
5. ተጫራቾች ለሚሰጡት አገልግሎት ነዳጅ፣ ቅባት እና ማንኛውም ወጪ በራሱ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
6. የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ/ከተዘጋ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
8. ተጫራቾች የሚጫራቱበትን እቃ/አገልግሎት የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ በሚያስኬደው መንገድ ሀዩንዳይ ፊት ለፊት በሚገኘው ሃና ፉሪ ግንባታ ሳይት ውስጥ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-66-42-82-98/ 09-12-00-72-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
