Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ : ኦሮሚያ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0471160012
  • Website
  • Deadline07 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-07 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Construction Works

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የሥቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ የሚሰራ ከአዲስ ከተማ ነሴ ቀበሌ 17 ኪ.ሜትር እና ከሁላሁኬ ኢሉ ቀበሌ 15.8 ኪ.ሜትር የመንገድ ጥገና ሥራ ሕጋዊ በመስኩ የተሰማሩ ደረጃ RC 1, RC-2. RC-3, RC-4 እና RC-5 ደረጃ ያላቸው ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በሠዓት አወዳድሮ የመንገድ ጥገና ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የሥቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ የሚሰራ ከአዲስ ከተማ ነሴ ቀበሌ 17 ኪ.ሜትር እና ከሁላሁኬ ኢሉ ቀበሌ 15.8 ኪ.ሜትር የመንገድ ጥገና ሥራ ሕጋዊ በመስኩ የተሰማሩ ደረጃ RC 1, RC-2. RC-3, RC-4 እና RC-5 ደረጃ ያላቸው ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በሠዓት አወዳድሮ የመንገድ ጥገና ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች/ኮንትራክተሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

መስፈርቶቹም:-

    1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የአመቱን ግብር የከፈሉና ዋናና ቅጂ መረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
    2. ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    3. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰረተ ቼክ CPO 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉ።
    5. ጠቅላላ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የፈዴራል መንግስት የተደነገገውን የግዥ ሕግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው።
    6. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፤ ለወደፊትም በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ በሚካሄደው በመንግስት የግዥ ጨረታ አይሳተፉም:: ለጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም፡፡
    7. በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ ማሽኖች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    8. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ መለወጥ፣ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መውጣት አይችሉም፡፡
    9. ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላይ መግለጫ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት ቀን (5) ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
    10. ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማና አድራሻ ማህተም መጥቀስ አለባቸው፡፡
    11. የጨረታውን ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
    12. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት የሰነድ ሽያጭ ይከናወናል፡፡
    13. የጨረታው ሰነድ አቅራቢ ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት በ22ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
    14. የተሰረዘ የተደለዘ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
    15. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
    16. ዘግይቶ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    17. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ዝርዝር ጠቅላላ መስፈርቶች በጨረታ ሰነድ ላይ ያሉ መሆናቸውን እንገልፃለን፡፡
    18. የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል እና የቴክኒክ ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች ለየብቻቸው ታሽጎው በተጨማሪም CPO ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ጥቅል በትልቅ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    19. ስለጨረታው የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር፡- 0471160012 /0950525419 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
    20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender