Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address ደብረ ማርቆስ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-771-66-91
  • Websitehttp://www.dmu.edu.et/
  • Deadline19 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2025-10-19 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Rent

ዋናው ግቢ ካፌ አገልግሎት የሚውል ሀንፃ ኪራይ ሴቶች ዶርሚታሪ አካባቢ የሚገኝ ህንፃ ቁጥር 555 ዋናው ግቢ ካፌ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ኪራይ ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ጀርባ የሚገኝ ህንፃ ቁጥር 856 ጤና ካምፓስ ላይ ለካፌ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ቁጥር 10 (ግራውንድ ብቻ) ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የዋጋ ተመን መሰረት መስራት (አገልግሎት መስጠት ለሚችሉ ተወዳዳሪዎች ለ3 (ሶስት ዓመት) የሚቆይ ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)


የካፌና መዝናኛ አገልግሎት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ብግጨ 01/2018

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ እና በጤና ካምፓስ ውስጥ የሚገኙ ለተማሪዎች የካፌ እና መዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎችን፡-

ሎት-1. ዋናው ግቢ ካፌ አገልግሎት የሚውል ሀንፃ ኪራይ ሴቶች ዶርሚታሪ አካባቢ የሚገኝ ህንፃ ቁጥር 555

ሎት-2. ዋናው ግቢ ካፌ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ኪራይ ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ጀርባ የሚገኝ ህንፃ ቁጥር 856

ሎት-3. ጤና ካምፓስ ላይ ለካፌ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ቁጥር 10 (ግራውንድ ብቻ) ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የዋጋ ተመን መሰረት መስራት (አገልግሎት መስጠት ለሚችሉ ተወዳዳሪዎች ለ3 (ሶስት ዓመት) የሚቆይ ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በቀረበው ማለትም፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው ንግድ ፈቃድና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ህንፃ (ካፌ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማስያዝ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከአንድ በላይ ካፌ እና ሬስቶራንት መጫረት አይችልም።
  4. በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት እንዲሁም ሱቆችና በሌሎች መገልገያዎች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች መጫረት አይችልም።
  5. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ለካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት የሚውሉ ሙሉ ዕቃዎችን ይዞ መምጣት ይጠበቅበታል።
  6. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን የ3 ዓመት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት።
  7. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 014 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደ/ማ/ ዩኒቨርሲቲ 1000017980517 በማስገባት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  8. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 014 ይከፈታል።
  10. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 09 21 06 15 26 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

Save Tender