Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
  • Address ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዋናው አደባባይ ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 202 ፡ ሀረር ከተማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 02566666994
  • Website
  • Deadline06 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ለሀረር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስፖርት ትጥቅ እና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ለሀረር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስፖርት ትጥቅ እና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን ግዢ ለማከናወን የወጣ ጨረታ

  1. ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ህጋዊ እና የሚያስፈልገውን መስፈርት የሚያማሉ ተጫራቶችን በተጠቀሰው ስራ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
  2. ጨረታውን የሚያከናውነው (LCB) የግገዢ ዘዴን በመጠቀም ሲሆን የስፖርት ትጥቅን እና ተዛማጅ ቁሳቁሶችን ማቅረብ የሚችል የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
  3. አቅራቢው በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃድ ያደሰ እንዲሁም የግብር ከፋይነት (ቲን ነምበር) መለያ ቁጥር ያለው።
  4. ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰአት ጠዋት 2፡00 - 6፡30 እና ከሰአት 8፡00 - 11:00 በመኘት መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  5. የጨረታ መመዘኛ መስፈርቶችን የፋይናንስ፣ የቴክኒክ እና ህጋዊ እውቅና ሌሎችም ይካተታል ፡፡
  6. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን መስከረም 24/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2018 ዓ/ም ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ በማቅረብ በአማረኛ ቋንቋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በጽሁፍ በማስመልከት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች በተጠቀሰው ሙያ የተሰጣቸውን ፍቃድ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጂናል፣ እና ኮፒውን በመለየት እና ለየብቻ በማሸግ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን የሎት ስም እና አድራሻ በመፃፍ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 ማስገባት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና የሚሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይችላሉ።
  9. የተጫራቾች ሃላፊ ወይንም ህጋዊ ውክልና ያለው እካል በጨረታው ሰነድ ሁሉም ገፆች ላይ መፈረም ይኖርበታል፡፡ ሃላፊነቱ ወይም ውክልናው በጹሁፍ ማረጋገጥ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች ባሉበት የጨረታ ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ መካከል ልዩነት ቢኖር ኦርጂናል ገዢ ይሆናል።
  11. የጨረታ ሰነዱ መስከረም 26/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ወይንም ከተጠቀሰው ቀን እና ሰአት በፊት ማስረከብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተውም መስከረም 30/2018 ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ጨረታ ተሳታፊዎች እና ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚፈለገው ኮፒ መጠን የሚያስገቡ ሆኖ የሚከተሉትን የያዘ መሆን አለባቸው። እነርሱም - የተፈረመ ፅሁፍ ማመልከቻ - የዋጋ ዝርዝር፤ የተሞላ የነጠላ ዋጋ፣ ጠቅላላ ድምር፣ ስለ ተጫራቹ ዝርዝር መረጃ
  13. ከላይ የተጠቀሱት ቀናት በአል ወይንም ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0256666699 በመደወል ማነጋገር ይቻላል፡፡
  15. ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ የጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዋናው አደባባይ ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 202።

 

ስልክ 02566666994 ፋክስ ቁጥር -0256660666 ፖስታ 272

 

የሀ/ህ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

 

Save Tender