Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 16/2018

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅጹ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ መስከረም 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

በመሆኑም፡-

  1. በተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
  2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
  4. ተጫራቾች የተሸከርካሪውንና የዕቃዎች የግልፅ ጨረታው ሠነድ ከሐሙስ መስከረም 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ተሽከርካሪዎች ወይም ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE አዲስ አበባ በሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤት

የጨረታ አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

የእቃ ግልጽ

እስከ 04/02/2018 ዓ.ም

05/02/2018 ዓ.ም 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

የተሽከርካሪ ግልጽ

እስከ 04/02/2018 ዓ.ም

05/02/2018 ዓ.ም 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ፡- 011-4-70-85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender