Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ6ኛ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት፣ የሥልጠኛ መርጃ እና የጽሕፈት ዕቃዎች፣የህሙማን ቀለብ፣የማሽነሪ፣ የጀኔሬተር እና የአፊስ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ6ኛ ዕዝ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- የኛ ዕዝ ግጨ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ6ኛ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት

 ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ፦

1. የፅዳት፣ የሥልጠኛ መርጃ እና የጽሕፈት ዕቃዎች፣

2. የህሙማን ቀለብ፣

3. የማሽነሪ፣ የጀኔሬተር እና የአፊስ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች ሲሆኑ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደርየሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚህ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ2:30 እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 11፡00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሆለታ 6ኛ ዕዝ ጠ/መምሪያ በሚገኘው ግዥ ከፍል ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ለተከታታይ አስርቀናት አየር ላይ ውሎ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆለታ ሳዳሞ ኖከ ማደያ ፊት በፊት የመምሪያ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ግቢ ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡-09-13-93-21-20/ 09-18-43-40-27/

09-13-63-45-62

በሀገር መከላከያ ሚ/ር የ6ኛ ዕዝ ጠ/መምሪያ

Save Tender