Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፤

  • ሎት 1፡- የጉልበት ስራ
  • ሎት 2፡- የህትመት ስራዎች
  • ሎት 3፡- ጥገና
  • ሎት 4፡- ስቴሽነሪ ዕቃዎች
  • ሎት 5፡- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማናኛውም የአገር ውስጥ ተጨራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ፋይናንስ ዳይሮክቶሬት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በዝመንት ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናል ዶክመንት እና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1፣2፣ እና 3 ሎት ሆኑትን ብር 5,000 /አምስት ሺ ብር/ ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
  8. ጨረታው በ11 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጠዋት 3፡30 የሚከፈት ሲሆን ነገርግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች በሎት 2 የህትመት ስራዎች ላይ የሚጫረቱ የዕቃ ናሙና /sample/ የጨረታ ጊዜው ሳያልቅ የማቅረብ ግዴታ አላቸው።
  11. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ።
  12. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል፡፡
  13. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጨራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ፤ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማውቅ አለባቸው፡፡

አድራሻችን፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በዝመንት ቢሮ ቁጥር 5

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender