Tender Detail

Tender Details

  • Company የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112305111
  • Website
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-10-17 00:00:00
  • Categories Building Materials , Printing And Publishing , Construction Works , Hospitality Service

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ሎት 9 - የህንፃ ቁሳቁስ እድሳትና ጥገና፣ ሎት 10 - የተለያዩ የህትመት ስራዎች፣ ሎት - 11 የሰራተኛ መስተንግዶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-002/2018

 

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ሎት 9 - የህንፃ ቁሳቁስ እድሳትና ጥገና፣ ሎት 10 - የተለያዩ የህትመት ስራዎች፣ ሎት - 11 የሰራተኛ መስተንግዶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  1. በየዘርፉ የተሰማሩትን ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀው ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት ሎት 9 - 2,500 ብር፤ ሎት 10 - 400.00 ብር፤ ሎት 11 – 5,136.00 በቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስያዝ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ /CPO/ ያልያስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በት/ቤቱ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት ለዚህ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. የጨረታ ሳጥን በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
  8. ለህትመት የተጫረቱ ተጫራቾች ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ /ተጫራች/ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
  9. የጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚያገኙት ባመረተው ምርት እና በምርቱ ላይ እሴት በጨመሩት ብቻ ሲሆን ሌሎች እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው CPO አስይዘው ይወዳደራሉ።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ት/ቤቱ የሚሰራውን ስራ ብዛት 20% የመጨመር /የመቀነስ/ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. የጨረታው አሸናፊ መሆንዎ ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% CPO በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011-2-30-51-11

 

የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender