በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ፌሮዎችንና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ፌሮዎችንና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዛላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ። ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በዕለቱ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዕለቱ በ8፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል። መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በተባለው ቀንና ሠዓት የሚከፈት መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ሙሉውን ክፍያ ፈጽሞ ዕቃውን የማያነሳ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይወረሳል።
- የጨረታ ሠነዱ በመ/ቤቱ ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስቁ 09-16-46-01-49
09-13-60-02-90
በጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ጋልማ፤
