የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመደበኛና የክረምት ኮርስ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የምግብ ጥሬ ዕቃዎችን በሎት በተከፋፈለው መሠረት በነጠላም ሆነ በጠቅላላው ሊያቀርቡ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የኮንትራት ውል ስምምነት በመዋዋል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Gambella Teachers Education and Health Science College (የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመደበኛና የክረምት ኮርስ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የምግብ ጥሬ ዕቃዎችን በሎት በተከፋፈለው መሠረት በነጠላም ሆነ በጠቅላላው ሊያቀርቡ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የኮንትራት ውል ስምምነት በመዋዋል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ሎት አንድ - ሁለተኛ ደረጃ ጤፍ የተፈጨ፣
ሎት ሁለት - ጥራጥሬዎችና የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች፣
ሎት ሦስት - ፍርኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይትና ስኳር፤
ሎት አራት - የሥጋ አቅርቦት ሆኖ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመስከቱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
- የ2017 ዓ.ም ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ስለመኖራቸው ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኮሌጁ ግዥና ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000 (አሥር ሺህ ብር) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አቅርበው በደረሰኝ ማስያዝ ወይም ከጨረታ ሰነዱ ወይም ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን ነጠላ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒውን ይዘው በመቅረብ በኮሌጁ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ በአጋጣሚ 16ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን የማይሆን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 047-5-51-02-93 ወይም በአካል ቀርበው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
