Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline22 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security17,000 .00
  • opening date2025-10-22 00:00:00
  • Categories Vehicle tire

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ላሉት የመንግስት ተሽከርካሪ መኪኖች የመኪና ጎማ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ለሁለተኛ ጊዜ ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ላሉት የመንግስት ተሽከርካሪ መኪኖች የመኪና ጎማ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች የሚከተሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. የግዥ መጠን ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታከስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ 200 ብር (መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚያው በ16 ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል፡፡

9. የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሺጎ በተመሳሳይሰዓት ይከፈታል፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ለመኪና ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግ አለበት፡፡

14. ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን እንዲያውቁትና የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅበዎት መሆኑን አይዘንጉ፡፡

15. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

ወግዲ 

Save Tender