Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline20 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-20 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Wood And Wood Working , Raw Materials , Industry And Factory

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕለይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው። ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓውደር /Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


 

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕለይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው። ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓውደር /Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

  1. በትክክለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ እና ስድስት ወር ያላለፈው ጨረታ ለመሣተፍ የሚያበቃ የገቢዎች የጨረታ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው።
  3. የሻት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡
  6. ተጫራቾች ለግሉ ፓውደር ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  8. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
  9. ማንኛውም ተጫራች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንታቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን/ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
  11. የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡
  12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፣
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  14. ከተጠቀሰው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡
  15. አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረከባል፡፡
  16. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 36 84 37 ደውለው ይጠይቁ።

 

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ደ/ብርሃን

 

Save Tender