በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት በአስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የአስተዳደር ህንጻ ውስጥ ያሉትን ክፍሎችን መታደስ የሚገቡትን ማሳደስ እና የአስተዳደር ግቢ ውስጥ መጸዳጃ ቤት እና በጓሮ በኩል የመኪና መግቢያ በር ማስራት ፈልጎ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ እንድናወዳድር ጠይቀውናል።
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መሰያ ቁጥር ግ/003/17
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት በአስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የአስተዳደር ህንጻ ውስጥ ያሉትን ክፍሎችን መታደስ የሚገቡትን ማሳደስ እና የአስተዳደር ግቢ ውስጥ መጸዳጃ ቤት እና በጓሮ በኩል የመኪና መግቢያ በር ማስራት ፈልጎ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ እንድናወዳድር ጠይቀውናል።
በዚሁ መሰረት
የሰራወው ሁኔታና ቦታ ጌሻ ወረዳ አስተዳደር ግቢ
ሎት 01 የአስተዳደር ህንጻ ዕድሳት በወጣወው የጨረታ ዶክሜንት መሰረት
ሎት 02 የአስተዳደር ግቢ ውስጥ መጸዳጃ ቤት መስራት እና በጓሮ በኩል የመኪና መግቢያ በር መስራት በወጣው የጨረታ ዶክሜንት መሰረት
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
-
ደረጃ ሰባት ( 7 ) እና ከዚያ በላይ የሆነ / B.ር ወይም G.C/ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያለው፡፡
-
የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ፡ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል ፣
-
የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፣ ቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ህጋዊ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
-
ከ2016 ዓም ጀምሮ የወሰደውን ግንባታ ስለማጠናቀቁ ከሰራበት መ/ቤት ማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል
-
ለመንግስት 2 በመቶ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፣
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለሃያ /20/ተከታታይ ቀናት በጌሻ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ከፍል ተጫራቾች ለግንባታው በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች
ለሎት 01 ቴክኒካል ኦርጅናል ለብቻ ፣ ፋይናንሻል ዋናውንና ሁለት ኮፒውን
ለሎት 02 ቴክኒካል ኦርጅናል ለብቻ፣ ፋይናንሻል ዋናውንና ሁለት ኮፒውን ለየብቻ የግንባታውን ስም በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛ ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
-
ተጫራቹ ድርጅቱ አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ስራ ሂደት ቢሮ በ 21ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
-
ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
-
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል።
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ ለሚወዳደሩበት ለሎት 01 15,000 ብር ለሎት 02 10,000 ብር ለየብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደ/ምዕ /ኢ/ክ/መ በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ ኢ/ ስ/ ጽ/ ቤት
