የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የዓይን መነጽር ሥራ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/08/SIG/2018
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የዓይን መነጽር ሥራ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቶች ህጋዊ ለ2017/18 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ: ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-8፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ሬሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251115516271 ወይም 115-500417
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ከሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
