የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/03/2018 ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/03/2018 ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ድርጅቶች ዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ውል ገብቶ በታባለው ጊዜ ውስጥ ጎማውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /መቶ/ በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን የራሳቸውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን እና የጎማው የቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን ዶክመንቱን ተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 10/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ /0949445729 /0910622700/0919519951/0946653304
አድራሻ ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
