Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
  • Address ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118 34-09-79
  • Website
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለህትመት 20,000 (ሃያ ሺ ብር)፣ ለመኪና ኪራይ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለዲኮር መድረክ እና ለድንኳን ኪራይ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር)፣ ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለጉልበት ስራ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-17 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Plastic Raw Materials And Products , Printing And Publishing , Vehicles Rent , Event Organizing And Planning , Labour Outsourcing Services , Rent , Decor Work

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰው የአገልግሎት ግዥ ለ2018 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰው የአገልግሎት ግዥ ለ2018 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1. መኪና ኪራይ
  • ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 3. ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ
  • ሎት 4. የህትመት ስራ አገልግሎት
  • ሎት 5. የጉልበት ስራ

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ። በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን፣ ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት ህትመት 20,000 (ሃያ ሺ ብር) መኪና ኪራይ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) ኤሌክትሮኒክስ ጥገና 10,000 (አስር ሺህ ብር) የጉልበት ስራ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው፡፡
  6. የተሻለ እማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. እቃው ወይም አገልግሎቶች ሊጨምርም ሊቀንስም የሚችለው 20% ብቻ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- ሙሉ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገፁ ፊርማ ተደርጐበት መመለስ አለበት ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

2. ለህትመት ስራ ሳምፕል መቅረብ አለበት

አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02

 

ስልክ ቁጥር፡- 0118-34-09-79

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር

 

Save Tender