አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ 2018 ዓ/ም ለመደበኛ እና አጫጭር ስልጠና አሰልጣኞች የቀለብ አገልግሎት የሚውል ሎት1. የእህል እና ጥራጥሬ፣ ሎት 2 ምግብ ማጣፈጫ (ባልትና ውጤቶች) ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ፣ ሎት 3 ማገዶ እንጨት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Asosa Agricultural TVET College (የአሶሳ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ 2018 ዓ/ም ለመደበኛ እና አጫጭር ስልጠና አሰልጣኞች የቀለብ አገልግሎት የሚውል ሎት1. የእህል እና ጥራጥሬ፣ ሎት 2 ምግብ ማጣፈጫ (ባልትና ውጤቶች) ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ፣ ሎት 3 ማገዶ እንጨት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በዚህ ንግድ ሥራ ዘርፍ ለመስራት የሚያስችላችሁ ህጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑ የ2017/2018 ዓ/ም ግብር የከፈሉ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (VAT) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በግልጽ የመወዳደሪያ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት ሠነዶቻቸውን አሪጅናልና ፎቶ ኮፒን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 8፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ድረስ በማምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ የሚሞላው ኮሌጁ በሰጠው እስፔስፊክሽን ዝርዝር ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ልክ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8:30 ሰዓት ላይ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ አሁድ /በዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም፣
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 200 የማይመለስ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ለተከታታይ 15ኛው ቀን አሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት ሥ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት ከታወቀ ባንክ ጋራንቲ ወይንም ሲፒኦ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 2 ፐርሰንት ሲፒኦ ካላቀረበ ወይም ከ2 ፐርሰንት ያነሰ ከሆነ ከውድድሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይሰረዛል፣
- ኮሌጁ አሸናፊ ድርጅት የሚመርጠው በእያንዳንዱ ዕቃ ዝቀተኛ ዋጋ እንጂ በጠቅላላው ድምር ዋጋ አይደለም።
- አሸናፊዎች የየውል ማስከበሪያ ያሸነፉበት 10% በማስያዝ ማሸነፉ ከተገለፀላቸው በ5 ቀናት ውስጥ ውል መግባት አለባቸው።
- አሸናፊዎች እቃውን የሚያስረክቡት ለሎት 1 ፤ሎት 2 ፣ሎት 3 በአሶሳ ግ/ት/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ውስጥ ባለው መጋዘን ይሆናል፣
- ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ እና ከተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታ ሂደት አስተጓጉልም፣
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት የተሰጠው ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ፌስቡክ ገጽ Asosa Agricultural TVET College ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 0911106356/0917176304/0924974707
የአሶሳ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
