Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0919141737
  • Website
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityሎት1 እና ሎት2 50,000 (ሀምሳ ሺህ)፣ ሎት 3 100,000 (መቶ ሺህ)
  • opening date2025-10-18 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Electronics Materials

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ኤላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት2 የሞተር ሳይክሎች፣ ሎት3 ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ኤላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት2 የሞተር ሳይክሎች፣ ሎት3 ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

  1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት (ቲን ነምበር) የምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. በስራ ዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም 2016 እና 2017 ዓ.ም ከመንግሥት መስሪያ ቤት ወይም ከታወቀ ድርጅት በማቅረብ መወዳደር ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ሎት1 እና ሎት2 50,000 (ሀምሳ ሺህ)፣ ሎት 3 100,000 (መቶ ሺህ) ብር ከታወቀ ባንክ በ/CPO/ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኮንታ ዞን አላ ሀንችኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ 15ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ኤላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ዶክመንቶች በመግዛት በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል አንድ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል አንድ እና ፋይናንሻል ኮፒ በድምሩ ሶስት ፖስታ በማሸግና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ኤላ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ንብረቱን እስከ ኮንታ ዞን አላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በማምጣት እና ሎት3 ጨረታውን አሸንፈው ውል በመግባት ንብረቱን እስከ ኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት በከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ አዲሱ ህንፃ ላይ የተጠየቀውን ዕቃ በሙሉ በመግጠም ማስረከብ አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራቾች ሎት3 ላይ ለመሳተፍ የዕቃ ናሙና ካላቀረበ ወደ ፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም። ተጫራቾች ለመካፈል የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ ላይ እንደሆነ በምታቀርቡት ሠነድ ላይ እና ፖስታ ላይ በትክክል ለይታችሁ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  9. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፀበትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋል። አሽናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. የአገልግሎት ግዥ ከ10,000 ብር በላይ 3% ያስከፍላል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር- 0919141737 // 0917980655/09179900606

አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 85 ኪሜ ርቀት ላዶ በጨዳ ከተማ አስተዳደር ግቢ ይገኛል።

 

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender