በማዕከላዊ ኢትዮጰጵያ ክልል መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በመደበኛና በካፒታል በጀት ዓመት በአዲስ ዘመን ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 1ኛ የጽህፈት መሣሪያ 2ኛ የሞተር ሳይከሎች ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
በድጋሚ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጰጵያ ክልል መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በመደበኛና በካፒታል በጀት ዓመት በአዲስ ዘመን ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 1ኛ የጽህፈት መሣሪያ 2ኛ የሞተር ሳይከሎች ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ በዘርፉ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር (ONLINE) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 10000 ብር ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን ማስፈርና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
5. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምስራቅ ጉራጌ ዞን/ፋ/ መምሪያ በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁዛ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ላይ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ተጽፎ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ በምስራቅ ጉራጌ ዞን/ፋ/ መምሪያ ግዥ ከፍል ላይ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ /የህዝብ በዓል/ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል በምስራቅ ጉራጌ ዞን መምሪያ ግዥ ከፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከታወቀ ውል ከገባ በኃላ ንብረቱ እስከ መስሪያ ቤታችን ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር/ 0916839798
በማዕከላዊ ኢትዮጰጵያ ክልል መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሩይናንስ መምሪያ
