በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዳባት ወረዳ አስተዳደር የስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት /DRDIP-11/ በ2018 ዓ.ም ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለወቅን ከተማ የውኃ አቅርቦት ስራ አገልግሎት የሚውል ፓምፕ እና አክሰሰሪዎችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ የወቅን ከተማ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዳባት ወረዳ አስተዳደር የስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት /DRDIP-11/ በ2018 ዓ.ም ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለወቅን ከተማ የውኃ አቅርቦት ስራ አገልግሎት የሚውል ፓምፕ እና አክሰሰሪዎችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፤
- ጨረታው የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ነው።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ስለ ዕቃው ዝርዝር ሁኔታ ለማወቅ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በዳባት ወረዳ አስተዳደር ግብርና ል/ጽ/ቤት በመምጣት በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለ2018 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተእታ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ የተ.እ.ታክስን ጨምሮ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መመዘኛዎች/ መስፈርቶች እና የተጫራቾች መመሪያ ያሟላ ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ይሆናል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናሺያል ሰነድ ኮፒ እና ኦሪጅናል ሰነድ በማዘጋጀት በፖስታ አድርገው በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ፖስታ ለብቻ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዳባት ወረዳ ከሚገኘው የግብርና ጽ/ቤት በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ኮሚቴ አባላት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የውድድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ፊርማና ማህተም መኖር ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይንም በጽሁፍ የጨረታው ጊዜ ሊያበቃ 3 ቀናት እስኪቀረው ድረስ መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቹ ቢያሸንፍ ፓምፑን ዳባት ወረዳ ወቅን ከተማ የውኃ ስራ ቦታ ማዕከል አጓጉዞ በማድረስ እና ፓምፑን አስተክሎ ስራ መጀመሩን ሲረጋገጥ ከፍያው የሚፈጸምለት ይሆናል።
- የክሬን ኪራይ እና የኤሌክትሮ መካኒካል ባለሙያ ወጭ ተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የጨረታውን መጠን 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-1-13-00-10 መደወል ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ የወቅን ከተማ
