Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሱሉልታ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address ሱሉልታ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0914990505
  • Website
  • Deadline29 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security40,000.00
  • opening date2025-10-29 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials , Electronics Materials , Cloth And Shoes

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ከተማ ወረዳ ፍረድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለፍርድ ቤታችን የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዘት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሱሉልታ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ከተማ ወረዳ ፍረድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለፍርድ ቤታችን የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዘት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) ብር ከሱሉልታ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በ21ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥን ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዳቸቻው ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከከል ጽህፈው መፈረም አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የሚቀረበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የተጻፈ መሆን አለበት፡፡

8. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ ሲቀርቡ (ለመሳተፍ) ሙሉ የኦዲት ሪፖርት የ2017 ዓ.ም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የምትወዳደሩበት የእቃ አይነት ላይ ሳምፕል (sample) ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ምከንያቱም የምትወዳደሩት ባቀረባችሁ sample ስለሆነ፡፡ Sample የደንብ ልብስ፣ እስቴሽነሪ፣ የፅዳት ቋሚ እና አላቂ ሲሆን፣ ኤሌከትሮኒከስ እና ፈርኒቸር በፎቶ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

10, ግዥው ከ20,000.00 ብር በላይ ከሆነ 50% ቫት ጽ/ቤቱ ይቆረጣል፡፡

11, በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያሰያስዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (Price validity date) ከጨረታው መከፈቻ ዕለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ(Delivery time) መግለጽ ይኖርባቸዋል።

 

13. አሸናፊዎች እቃው እስከ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ :-09-21-80-18-13/09-11-59-73-04/09-14-45-89-23

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሱሉልታ ከተማ ፍርድ ቤት

Save Tender