በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደርቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-02/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደርቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-
ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ
ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3. የውሃና የግንባታ ዕቃዎች
ሎት 4. ሲሚንቶ
ሎት 5. የእንስሳት መድኃኒት
ሎት 6. የእንሰሳት የህክምና መሳሪያዎች
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው::
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፡፡
4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የግዥ መጠኑ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዘጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
6. ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን 19 ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. የግዥ መጠኑ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ለመንግስት 3% የሚከፍሉ መሆኑን ይወቁ ::
8. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ከተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ ለሎት 1ብር60000 /ስልሳ ሺህ ብር/፣ ለሎት-2. ብር 5000/አምስት ሺህ ብር/፤ ለሎት-3 ብር 50,000/በር ሃምሳ ሺህ ብር፤ ለሎት-4, ብር 30000/ሰላሳ ሺህ ብር ለሎት-5. ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ፡ ለሎት-6. ብር10,000/ብር አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ከጨረታ ውጭይሆናል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘውትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
12. ለሁሉም ሎት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡15 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው ግልፅና የማያሻማ መሆን አለበት፡፡
14. ለፅህፈት መሳሪያ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ በግዥ ፈፃሚው መ/ቤቱ የቀረበውን ናሙና ማየት አለባቸው፡፡
15. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ የሚታሸግበትን ፖስታ ጨምሮ በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ገፆች ላይ የጨረታውን ዓይነት፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡.
16. ማንኛውም ተጫራቶች አንድ ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአርጅናሉና ኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ገዥው ኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡
17. ማንኛውም ተጫራች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ በመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት፡፡
18. ተጫራቶች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ፣ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
19. መ/ቤታችን አሸናፊውን የሚመረጠው በሎት ጥቅል ዋጋ ድምር ዝቅተኛ የሞላውን አሸናፊ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በሎት ከተገለጸው የእቃ ዝርዝር ውስጥ ለይቶ መሙላት ከጨረታ ውጭያደርጋል፡፡
20. ከሎት አንድ (1) እስከ ሎት አራት (4) በተጠቀሰው ውስጥ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እታ ማንኛውንም ወጭ ችሎ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
21. ማንኛውም ተጫራች በለላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
22. ማንኛውም አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉትን እቃ ገቢ በሚሆንበት ጊዜ ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ እና የታሸጉ እቃዎች ተፈተውና ታይተው ችግር ቢኖርባቸው የማንቀበል መሆኑን እና የሚያቀርባቸው እቃዎች ጥራት ያለው መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
23. መ/ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ የተጠየቀውን እቃ ብዛት 20% ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
24. የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን በበዓላት ቀን፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
25. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
26. ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033-441-05-73 ወይም 033-441-02-67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የተን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
