በልደታ ክ/ከ/ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 001/2018 መሰረት የተለያዩ እቃዎቸን መግዛት ይፈልጋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከ/ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 001/2018 መሰረት
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት ሥራዎች
- ሎት 4 የትምህርት መሣሪያዎች
- ሎት 5 የፅዳት አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት 7 ቐሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 8 ቐሚ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች
- ሎት 9 የጥገና እቃዎች እና የውጪ የብረት በር ሥራ እንዲሁም የአሸንዳ ጥገና ቴራዞን ማንጠፍ
እንዲሁም የውጪ አጥር ቀለም መቀባት
በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈሉ፡፡ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ ከነቫቱ መጠቀስ አለበት፡፡
3. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00-10:00 ሠዓት በፋ/ግ/ን/አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት በእያንዳንዱ ሎት 2 (ሁለት ፐርሰንት) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተወዳዳሪው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የግዢውን ግምታዊ ዋጋ 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናው ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፤ ካላቀረቡ ግን ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
7. ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
8. በጨረታው የሚቀርቡት ዕቃዎች የጥራት ደረጃውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በግዥ ጨረታው ላይ ከተጠየቀው ውጪ ናሙና ማቅረብም ሆነ ናሙናው ላይምልከት ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
ማሳሰቢያ:- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- በልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 ከኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ ጀርባ ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር ፡- 0113 -20- 28- 13 ወይም 0113-72-77-68
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
