Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡-01/2018

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 - የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጎማ፤

ሎት 2 - የተለያዩ የዳቦ ማሽን እና የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች፤

ሎት 3 - አላቂ የጋራጅ መርጃ ዕቃዎች፤

ሎት 4 - የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፤

ሎት 5 - የተለያዩ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፤

ሎት 6 - የተለያዩ የስልጠና መርጃ ዕቃዎች፤

በዚህም መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፤ የቫት ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት የምስክርወረቀት ያላቸውን ይጋብዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያና ዝርዝር ሰነድ የያዘ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በጅማ ከተማ ሳሪስ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከላዊ ዕዝ ግዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በ8:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-09-29-38-29-84/09-11-37-59-08

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር

የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

Save Tender