በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሠራተኞች የደንበ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት እቃዎች፣ የህከምና ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፤ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የላብራቶሪ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ግብአቶች ናቸው።በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3(ፋይናንስ ቢሮ) የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቻው ቀን በፊት ኦርጅናልና ደረጃውን የጠበቁ ለእያንዳንዱ ዕቃ አንድ አንድ ናሙና ለት/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) በየሎቱ የተጠቀሰውን ብር መጠን ሲፒኦ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሎት-1. የደንብ ልብስ፡- 26462.00
ሎት-2. አላቂ የቢሮ እቃዎች :-19086.00
ሎት-3. የሕትመት ዕቃዎች፡- 2600.00
ሎት-4. የሕክምና ዕቃዎች:- 2200.00
ሎት-5. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች:- 31675.00
ሎት-6. የፅዳት ዕቃዎች:- 29538.00
ሎት-7. ልዩ ልዩ ዕቃዎች:- 9887.00
ሎት-8 የምርምር ዕቃዎች : 4000.00
ሎት-9. ቋሚ ዕቃዎች- 15098.00
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ የዋጋ መሙያ ቦታ በግልፅ ቫትን ጭምሮ የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ በተጠየቀው ብዛት አባዝተው ያመጡትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሙሉ በሙሉ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍ በመጨረሻ ገፅ ሙሉ የድርጅታቸውን ስም፣ አድራሻ፣ እንዲሁም ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ለይቶ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።
8. የተጫራቾች ውጤት ተለይቶ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ።
9. የቅሬታ ጊዜ ካለፈ በኋላ የጨረታ አሸናፊዎቹ ተለይተው ከተገለፁበት ቀነ ገደብ ቀጥሎ ባለው ተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማሰያዝ ውል በመፈፀም እቃውን ማቅረብ አለባቸው።ያላሸነፉ ተጫራቾች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና ናሙና መውሰድ ይችላሉ።
10 አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው (በተጫራቹ) ትራንስፖርት ቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
11 መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ቸራሊያ ሳይደርስ በስተግራ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-4626451 / 011-4626324
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
