ዘመን ኮንስትራከሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ የፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት እና የውሃ ስርገት አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ጨረታ ቁጥር 08/2018 ለተለያዩ የፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት ጨረታ ቁጥር 09/2018 ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዳታ እና ቴሌ እና የትራፊክ መብራት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 10/2018 ዓ.ም ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጀነሬተሮ እና ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ጨረታ ቁጥር 11/2018 እና ጨረታ ቁጥር 12/2018 ግዥ ለመፈጸም ሕጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር
08/2018:09/2018:10/2018:11/2018 እና 12/2018
ዘመን ኮንስትራከሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
-
ለተለያዩ የፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት እና የውሃ ስርገት አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ጨረታ ቁጥር 08/2018
-
ለተለያዩ የፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት ጨረታ ቁጥር 09/2018
-
ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዳታ እና ቴሌ እና የትራፊክ መብራት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 10/2018 ዓ.ም
-
ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጀነሬተሮ እና ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ጨረታ ቁጥር 11/2018 እና ጨረታ ቁጥር 12/2018 ግዥ ለመፈጸም ሕጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
-
በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ያለው/ያላት፤
-
የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
-
የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 1 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ሕንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሊፍት እና ጀነሬተር 20 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የዕቃ አቅርቦቶችን እና የውሃ ስርገት አቅርቦትና ገጠማ የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) እንዲሁም ለጀነሬተር እና ሊፍት አቅርቦት እና ገጠማ እስከ 20ኛው ቀን (20 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦጅናልና ኮፒ በመለየት ባህር ዳር ዋናው ቢሮ ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ አቅርቦት እና ገጠማ ለሆኑት ከዚህ በፊት የውሃ ስርገት፣ዳታና ቴሌ፣ ጀነሬተሮች እና ሊፍቶች /አሳንሰሮች አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ በብቃት እና በጥራት ለመሥራታቸው የሚያረጋግጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማያያዝ ግዴታ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
-
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ባህርዳር-058-218-0538 /09-13-27-60-57/ 09-18-71-66-16
አዲስ አበባ ፡- ስልክ ቁጥር 0111265338/0930352410/0967994210
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
