Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ
  • Address ጎሮ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ያለው ህንጻ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security10,000 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Pharmaceutical Products , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጎሮ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት1 ህክምና እቃዎች እና መድሀኒቶች እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 02/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጎሮ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት1 ህክምና እቃዎች እና መድሀኒቶች እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር /100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 403 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

ሎት                         ሎት ዝርዝር                                የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1.                     የህክምና እቃዎች እና መድሃኒቶች             10,000

ሎት 2.                           ሪኤጀንቶች                                            10,000

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራኦች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ማስገባት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰአት ታሽጎ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ማሳሰቢያ ናሙና የማይቀርቡባቸው እቃዎች ውድቅ ይሆናሉ።
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. መስሪያ ቤቱ ለጨረታው ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመጨርም ሆነ መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑን አለበት ።
  12. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የጨረታ ሰነድ መግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  13. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ በየሎቱ የተጠቀሰውን ገንዘብ መጠን ማስያዝ አለባቸው።

አድራሻ፡- ጎሮ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender