Tender Detail

Tender Details


በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሎት 1 - አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ በሎት 2 -አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ በሎት 3 - አላቂ የጽዳትና ሌሎች ዕቃዎች፣ በሎት 4 - የደንብ አልባሳትና የስፖርት መምህራን ልብስ፣ በሎት 5 - የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በሎት 6 - ቋሚ የህትመት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የመጀመሪያ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ላ/ከ/ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሎት 1 - አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ በሎት 2 -አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ በሎት 3 - አላቂ የጽዳትና ሌሎች ዕቃዎች፣ በሎት 4 - የደንብ አልባሳትና የስፖርት መምህራን ልብስ፣ በሎት 5 - የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በሎት 6 - ቋሚ የህትመት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN number/ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ የተመዘገቡና ለመመዝገባቸውም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከመ/ቤቱ በወሰዱት የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጉልህ በሚታይ መልኩ ከቫት በፊትና ከቫት በኋላ ያለውን ዋጋ ፅፈው የድርጅቱ ተወካይ ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርገው በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለወሰዱትና ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በሚሞሉት አጠቃላይዋጋ ላይ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖባቸዋል።

4. ተጫራቾች ናሙና እንዲገባ በተጠየቁባቸው የእቃ አይነቶች ሁሉ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአንድ ሎት ብር 150.00 /ብር አንድ መቶ ሃምሳ በመከፈል ከመ/ቤቱ ረ/ፋ/ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛትና መውሰድ ይኖርባቸዋል።

6. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ ከሚያቀርቡት ወይም ተጨማሪ እሴት ጨምረው ከሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ውጪ የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው በሚወዳደሩበት ጊዜ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት የጨረታ ሰነድ መግዛት፣ የጨረታና የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቶች አሸናፊ ሆነው ለተጎኙባቸው እቃዎች የሞሉትን አጠቃላይ ዋጋ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የhow የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቶች ላሸነፉበት እቃዎች መ/ቤቱ ምንም አይነት የዋጋ ለውጥ ሳያደርግ ብዛቱን 20% ዝቅም ከፍም አድርጎ ሊያስተካከል ይችላል።

9. ተጫራቶች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግና በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 በመግኘት በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታ ሰነዱን የመመለሻ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

11. የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ከት/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የሚመለከታቸው ታዛቢ አካላት በተገኙበት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና/ወይም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።

12. ውል የተዋዋሉ አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ንበረት ማከማቻ ከፍል ውስጥ ማምጣትና ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ላፍቶ ታክሲ ማዞሪያ አካባቢ ከአዋሽ ባንክ ፊት ለፊት ባለው የኮብል ንጣፍ መንገድ ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር:-011-4-71-06-42/011-4-71-06-45/011-4-19-67-76

የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender