በአዲስ ከተማ ከፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ ከተማ ከፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-1/2018
በአዲስ ከተማ ከፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 - የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ፤
ሎት 2 - አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
ሎት 3 - አላቂ የትምህርት እቃዎች እና የላብራቶሪ እቃዎች፣
ሎት 4 - ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣
ሎት 5 - ቋሚ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር፣
ሎት 6 - ልዩ ልዩ መጽሀፍት እና ትራንስፖርት፣
ሎት 7 - የህትመት ስራዎች፣
ሎት 8 - የኮምፒውተር እና ፕሪንተር ጥገና፣
ሎት 9 - የመስታወት ጥገና፣
ሎት 10 - የመስተንግዶ አገልገሎት፣
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራች ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል::
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ማንኛውም ተወዳዳሪ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ አቅራቢነት 1 ዝርዝር /supplier list/ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
5. በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ 1 ያላላፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
6. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች የምትወዳደሩበትን እቃ የራሳችሁ ምርት /አምራች/ መሆናችሁን የሚገልጽና በአመረታችሁት ዕቃ ላይ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን።
7. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ከፍል የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
8. የጨረታ መዝጊያ ቀን ማስታወቂያው ከመጣበት በ10ኛው ቀን ላይ በ11:30 ሰዓት ታሽጎ የመከፈቻው ቀን በ11 ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ከፍል የሚከፈት ይሆናል። የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገኘው ዋጋ ማቅረቢያ ዋጋቸውን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም ፋይናንሻሉን ዋና እና ኮፒውን በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ከፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ማንኛውም ተጫራች መጫረት የሚችለው በሚመለከተው የንግድ ስራ ፈቃድ /ስራ ዘርፍ/ ብቻ ነው።
11. አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለባቸው:: በተጨማሪም ት/ቤቱ ከገዙት እቃዎች ላይ እንደእስፈላጊነቱ 20% የመጨመር ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ተጫራቶች ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. ሁሉም የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡ ሳምፕል ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14.ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ በባንከ በደጃዝማች ኡመር ሰመተርአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም CPO 0.7% በማሰራት ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
|
ሎት |
ሎት1 |
ሎት2 |
ሎት3 |
ሎት4 |
ሎት5 |
ሎት6 |
ሎት7 |
ሎት8 |
ሎት9 |
ሎት10 |
|
ብር |
9,000 |
10,900 |
7,000 |
11,200 |
12,600 |
3,500 |
840 |
2,450 |
1,750 |
6,300 |
ማሳሰቢያ:-
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቼከ ማስያዝ ከውድድር ውጪ የሚያስደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
- የግዥ መመሪያው ሰንድ ላይ በተጫራች መሞላት ያለባቸውን ክፍሎችን ሞልተው ማህተም ተደርጎ ተያይዞ መመለስ አለበት።
አድራሻ:- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አጣና ተራ ወረዳ 10 ጀርባ ወይም ሪንግ ሮድ ሆስፒታል ፊትለፊት ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-86-32/ 011-2-80-40-94
የደጃዝማች ዑመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
