Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0118 12 51 78
  • Website
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Catering And Cafeteria Services

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኝ ጽ/ቤት የተለያዩ ከባድ መኪና የጥገና ዕቃዎችና እና ሰርቪስ እንዲሁም ከሆቴል ውጭመስተንግዶ አልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን


ጨረታ ማስታወቂያ

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኝ ጽ/ቤት የተለያዩ ከባድ መኪና የጥገና ዕቃዎችና እና ሰርቪስ እንዲሁም ከሆቴል ውጭመስተንግዶ አልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የከባድ መኪና ጥገና እና ሰርቪስ እና እቃዎች

ሎት 2 የካፍቴሪያ መስተንግዶ

ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መጻፍ አለባቸው::

2. ተጫራቾች ድረ ገፅ (ዌብ ሳይት) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኋላ ደግሞ 25% የዋጋውን መጨመር ይችላል፡፡

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቶች ለሚጫረቱባቸው የመኪና ጥገና እና ካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች በሙሉ የመስሪያ ቤቱ ቴክኒከ ኮሚቴ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጐ ይወሰዳል፡፡

6. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1፡- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር /ሎት 2: - 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ከ/ሂ ቡድን ስም በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመከፈል በመንግስት የስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደርቡድን ቢሮ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ቴከኒከ ጨረታ ሰነድ _ አርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባትአለባቸው::

8. የካፒታል መጠናቸው ከብር 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ በላይ የሆኑ እና ተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 

9. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን በ11:30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

12. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

13. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ሁሉም ዋጋ መሞላት አለባቸው ያልተሞላ ዋጋ ከሆነ ከውድድር ውድቅ ይሆናል፡፡

14. ተጫራቾች በንግድ ፍቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው የተጫራቾች ማህተምና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል፡፡

15. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል እና እንደ ሁኔታው ለቀሪው በጀት አመት ውል ሊራዘም ይችላል፡፡

16. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው አገልግሎት ወይም ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡

17. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ዋጋ መሙያ ፎርማት ላይ የሚያስገቡትን ዋጋ ግዴታ መሙላት አለባቸው፡፡

18. ተጫራች አሸነፊ የሆኑባቸውን የመኪና ጥገና ዕቃዎች እና ሰርቪስ በራሱ ጥገና ቦታ ጠግኖ እና ሰርቪስ በማድረግ እንዲሁም ብልሽት ካጋጠመው ቦታ ወይም መንገድ በራሱ ከሬን በማምጣት ወደ ጥገና ቦታ መውሰድ ግዴታ የሚገባና እና የካፍቴሪያ መስተንግዶ በግቢ ውስጥ በሚፈለግበት ጊዜ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

19. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የከባድ መኪና ጥገና እንዲሁም የመንግስት ካፍቴሪያ መስተንግዶ የአገልግሎት ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸናፊው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118 12 51 78 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

Save Tender