Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን በጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም እወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን በጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም እወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

የእቃ ዝርዝር………………………………………………………………………………….. CPO መጠን በብር

ሎት1: የፅህፈት መሳሪያዎች………………………………5,000

ለት 2፡ የጽዳት እቃዎች…………………………………………………………………….5,000

ሎት 3 ደንብ ልብስ ግዥ…………………………………5,000

ሎት 4 ደንብ ልብስ ስፌት…………………………………5,000

ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ…………………………………….10,000

ሎት 6 ቋሚ የቢሮ እቃ…………………………………….5,000

ሎት 7 ቋሚ የህከምና እቃ………………………………….20,000

ሎት 8 አላቂ የሀክምና እቃ…………………………………10,000

ሎት 9 ልዩ ልዩ እቃዎች ……………………………………3000

ሎት10 ህትመት…………………………………………5000

ሎት 11 ሽንት ቤት እና የእጅ መታጠቢያ ……………………………………………….3000

ሎት 12 የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች ጥገና………………………………………………..1000

ሎት 13 ቋሚ የህክምና እቃዎች ጥገና……………………………………………………2000

በባንክ የከፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

እንዲሁም በደብዳቤ የምትወዳደሩ ተጫራቾች በጽህፈት ቤቱ የበላይ ሀላፊ የተፈረመ ህጋዊ ደብዳቤ በማስያዝ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

ስለዚህ የተጠየቁትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ለአንድ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለትመቶ) ብር እና በተጨማሪ ቋሚ የህከምና እቃ ጨረታ ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከጤና ፅ/ቤት የተሰጠዉን ስፔስፊኬሽን መውሰድ ያለባችሁ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ2፡30-11:15 የጨረታ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት

2 የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ በየ ዘርፉ ያላቸው መሆን አለበት

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ቫት የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላችው መሆን አለባቸው

6. የግብር ከፋይነት ቲን ሰርተፍኬት መቅረብ አለበት፡፡

7. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው::

8. ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት የሚወዳደርበትን የሎት አይነት በፖስታ ላይ መገለፅ አለበት፡፡

በተጨማሪ ቋሚ የሀከምና ዕቃዎችን የምትወዳደሩ ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴከኒከ መግለጫዎችን በተለያዩ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡

የሚወዳደርበትን ሎት በግልፅ በፖስታው ጀርባ ላይ ያልገለፀ ተጫራች አይስተናገድም ውድቅ ይደረጋል)።

ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡

* ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡

* እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅታችሁ ማህተም መኖር አለበት፡፡

መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

እያንዳንዱ ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ 20% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡

አድራሻ ለሚ ኩራት ከከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ከአያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው

መንገድ አያት ቁጥር 1 ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ስልከ ቁጥር 011-8690779 /011-8681387/

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ

Save Tender