Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ
  • Address የደሴ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0331118629
  • Website
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን 1.5%
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Machinery

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክ የሚሰራ የከተማ አውቶብስ እና ቻርጅ ማድረጊያ ማሽን መስፈርቱን ከሚያሟሉ ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክ የሚሰራ የከተማ አውቶብስ እና ቻርጅ ማድረጊያ ማሽን መስፈርቱን ከሚያሟሉ ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ድርጅቱ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል።

  1. በዘርፉ የተሰማሩና በዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው የተጨማሪ አሴት ታክስ ወይም /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፡
  3. በተሰማሩበት የስራ መስክ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ /ሰፐላይ ሊስት/ ላይ የተመዘገቡ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን ማሟላትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋውን 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኦሪጂናል እና የማይመለስ ኮፒ የስራ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ይዘው በቀረቡበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 የተጠቀሰው ቢኖርም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  11. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሆኖ ለመለየት አሻሚ ነገር መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለም ጨረታውን የሞላው አካል ስርዝ ድልዝ ስለመኖሩ መፈረም (ፓራፍ) ማድረግ ይኖርበታል፤
  12. የጨረታ መክፈቻው ቀን በዕለቱ ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
  13. አሸናፊ የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ ዕቃዎች በሙሉ በድምሩ /LOT/ ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢው ይሆናል፤ በዚህ መስፈርት መሰረት ለሁሉም ዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፤
  14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ ከተማ አስ/ገ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0331118629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የደሴ ከተማ አስ/ገ/መምሪያ

 

Save Tender