Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ አካባቢ በሚገኛው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ህንፃ 15ኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼይን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-38-98
  • Websitehttp://www.ethiopianelectricutility.gov.et/
  • Deadline08 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር)
  • opening date2025-10-08 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Hand Tools And Workshop Equipment , Mechanical Work and Materials

ተቋማችን የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተከትሎ ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)


 

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤስ/ፍፋግ/ግጨ-005/2018

 

ተቋማችን የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተከትሎ ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች ግዥ

500,000.00 (አምስት መቶ ሺ)

መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተቋማችን ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ስለጀመረ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች በሙሉ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች በመያዝ ወደ ተቋማችን ቢሮ ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በአካል በመቅረብ መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር ለመውሰድ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚስጥር ቁጥራቸውን ከወሰዱ በኋላ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥርነ1000068699332 በመከፈል ባንክ የከፈሉበትን የክፍያ ሰነዱን ስካን በማድረግ misrakfan@gmail.com ወይም getu3010@gmail.com በሚል ኢሜይል አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል።
  4. በመቀጠል በተቋሙ በዌብሳይት አድራሻ https://eeusrmvendorportal.ethiopianelectricutility.et/irj/portal ላይ በተሰጣቸው መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር በመግባት ማግኘት ይችላሉ።
  5. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ያገኘ ተጫራች የኤሌክትሮኒክስ ዘዴን በመጠቀም ምላሽ ለመስጠት ተቋማችን በሚያመቻቸው የስልጠና /training orientation/ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ስልጠናውን በመውሰድ መሆን ይኖርበታል።
  6. አድራሻ፡- ሜከሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-126-66-05/011-156-01-48
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <<ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY›› በሚል መሆን ይኖርበታል፣
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የኤሌክትሮኒክስ ግዢ የምላሽ አሰጣጥ ስርአትን በመከተል ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት መሆን ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርአትን በመከተል በኦንላይን ስለሚሆን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው መሰረት በአን ላይን ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦሪጅናል እና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙናውን ጨረታው በሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ንብ ባንክ 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በአካል ማቅረብ አለባቸው።
  11. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

 

Save Tender