Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ??/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጀምሮ በ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት (የስራ ቀናት)
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials , Electronics Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት 2 ኤሌከትሮኒከስ ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ፣ ሎት 4 ቋሚ መሰል እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት 2 ኤሌከትሮኒከስ ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ፣ ሎት 4 ቋሚ መሰል እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ

3. የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ያላቸው

4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው

5. የግዥው መጠን ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና ከዚያም በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለጽህፈት መሳሪያ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ፣ ለኤሌክትሮኒክስ 40,000/አርባ ሺህ ብር/ ፣ ለጽዳት እቃ 5000/አምስት ሺህ ብር/ ለቋሚ መሰል እቃ 10,000/አስር ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30/ሶስት ሰዓት ተኩል ድረስ/ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡

ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ከሰላሳ አንድ ተዘግቶ 4፡00/አራት ሰዓት /ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል፡፡

8. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል፡፡የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 የሰነድ ከፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መበቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

10, ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል፡፡

11. የጨረታው ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ማህተም የሌላቸው ተጫራቾች ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡

12. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡

13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ 06 ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender