Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ-ክህነት ጽ/ቤት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
  • Address መገናኛ ሾላ እልፍ ጸጋ ህንጻ 4ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251938644444
  • Website
  • Deadline08 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1,000,000 (አንድ ሚሊየን ብር)
  • opening date2025-10-08 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ እና የተለያዩ የራስ አገዝ የልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ-ክህነት ጽ/ቤት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ እና የተለያዩ የራስ አገዝ የልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ይፈልጋል። ገዳሙ ከመንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ የሚጠቅም አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎችንም አካቷል።

  1. ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ያቀርባሉ።
  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/
  • የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል ሚገልፅ የፅሁፍ ማስረጃ (ጊዜ ያላለፈበት መሆን ይኖርበታል)
  • የተ.እ.ታክስ /VAT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት
  • ተጫራቾች በታክስ ባለስልጣናት የተመዘገቡ እና የታክስ ማጽጃ ወረቀታቸውን ቅጂዎች ጨምሮ ትክክለኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት መቻል አለባቸው።
  1. ተጫራቾች ሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የግንባታ ሥራን ለማሰራት ቢያንስ GC-5/BC-5 እና ከዛ በላይ ህጋዊ የተመዘገበ ተቋራጭ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተናጠል ዋጋቸውን እና ጠቅላላ ዋጋቸውን ቫትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብር በግልጽ መግለጽ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1,000,000 (አንድ ሚሊየን ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው። የኢንሹራንስ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
  4. ተጫራቾች ጥያቄ ካላቸው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቀን 28/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዛኑ ቀን 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል በሁለት የተለያዩ ማህደሮች በማዘጋጀት ማስገባት ይችላሉ።
  7. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በታሸገ ቴክኒካል የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የቴክኒክ ምዘናውን በተሳካ ሁኔታ ያለፈ ኮንትራክተር ብቻ ለፋይናንስ ያለ ምዘና ግምት ውስጥ ይገባል። ቴክኒካል ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻው ዝርዝር መረጃ በመገኛ መረጃዎቻቸው ይነገራቸዋል።
  8. የሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ከታች በተቀመጠው አድራሻ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ መገናኛ ሾላ እልፍ ጸጋ ህንጻ 4ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ:- +251938644444 / +251918077957

 

Save Tender