Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር የቂ/ከ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት 001/2018 /2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር የቂ/ከ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት 001/2018 /2018 በጀት ዓመት የተለያዩ

ሎት 1፡ የፅህፈት መሳሪያ፣

ሎት 2፡ የጽዳት እቃዎች፣

ሎት 3፡ የደንብ ልብሶች፣

ሎት 4፡ የተለያዩ ቅርፃቅርጽና የህትመት ውጤቶችን፣

ሎት 5፡ ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣

ሎት 6፡ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች የመኪና ዘይትና ቅባቶች፡

ሎት 7፡ የተለያዩ የጥገና እቃዎች፣

ሎት 8፡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣

ሎት 9፡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ የጥገና ስራዎች እና

ሎት 10- የመስተንግዶ ግዥ (ውሀ/ ሌሎችም ወዘተ…በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ከሚሸጡበት ዋጋ 10% /አስር በመቶ/በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታከስን ያካተተ መሆን አለበት፣

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ የእቃው /አገልግሎት/ መጠንና ዋጋ Financial & Technical envelop/ በዝርዝር ተሞልቶ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት አለባቸው፤

 

6. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በነጋታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰባተኛ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል፤

7. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000009412399 በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ገቢ በማድረግና አድቫይስ ይዞ በመምጣት የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቂርቆስ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብርከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቢሮ የማስገባት ግዴታ አለባቸው፤

9. አሸናፊው ድርጀት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤

10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ 400 የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቄራ ኢትፍሩት ፊት ለፊት መንገድ ተሻግሮ ባለው መንገድ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ ቅድስት ታወር

ለማንኛው ተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር 011 4 70 16 63

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የቂርቆስ ክ/ከ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የፋይናንስና ግዥ የሥራ ሂደት

Save Tender