የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር
የአገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02
የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርያላቸዉ፣ የቫት ምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
2. ተጫራቾች በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/በሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና /Unconditional Bank guarantee/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺ/ ብር ማስያዝ አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነዱን ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ከኛ ፎቅ ፋይናንስ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ወይም በኮርፖሬሽኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር1000265163223 በማስገባት የባንክ እስሊፕ በማቅረብ ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተናጥል የምናወዳድር ይሆናል። የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ወጪ ያካተተ ይሆናል። የተሞላው ዋጋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት የፀና ይሆናል።
5. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለፁት ዕቃ የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል። በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ /ጋዜጣ) ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20/ሀያ/ ተከታታይ ቀናት በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው (ሃያኛው) ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ይከፈታል:: የመከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያ ይገለፃል።
ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 መደወል ይችላሉ::
አድራሻ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት
የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
