በሰ/ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ የመራኛ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት 1ኛ የውሀ እቃዎች እና 2ኛ የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
በሰ/ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ የመራኛ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰ/ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ የመራኛ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት 1ኛ የውሀ እቃዎች እና 2ኛ የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከፋይነት መለያ ቁጥር እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,0000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር /በመከፈል በሚ/ወ/ወ/ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በአዲሱ የንግድ ስራ መስጫ መደቦች እና በተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ ኮድ ቁጥር ለተሰማሩበት የስራ መስኮች የተገለጸው ትንታኔ መሰረት ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
5. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ /c.p.o/ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተበት የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቹ በማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በመራኛ ውሀና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል።
8. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት በመራኛ ውሀና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች እቃውን በመራኛ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት በሚገኘው ንብረት ክፍል ግቢ ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ 09 62 31 10 65/ 09 39 72 27 94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሰ/ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ የመራኛ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
