በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከነሙሉ የማጽጃ ግብአቶች የሚያቀርቡ ኤጀንሲዎችን እና በንፋስና ዝናብ ምከንያት የፈረሰ ጣሪያ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን አሟልቶ የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ የጨረታ ቁጥር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከነሙሉ የማጽጃ ግብአቶች የሚያቀርቡ ኤጀንሲዎችን እና በንፋስና ዝናብ ምከንያት የፈረሰ ጣሪያ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን አሟልቶ የሚሰሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሊራንስ፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ደብደቤ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁምየግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ıo ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በላይተከሉ ኬክ ቤት ጎን በሚገኘው ዊዝደም የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር መርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ላይ 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705/704 የግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ(C.P.O.) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenues Bureau Merkato No 2 Medium Tax Payers Branch Office) በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለሆኑት ከአደራጅ መስሪያ ቤት የጨረታ መወዳደሪያ ዋስተና ደብዳቤ ማጻፍ እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የፋይናንሻል ወይም የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ዋጋው ከነቫቱ ተሞልቶ ብቻውን በኦርጅናል እና ኮፒ (ዋናውና ቅጅ) ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ በድምሩ በአራት ኤንቨሎፕ ኦርጂናልና ኮፒውንወይም (ዋናውንና ቅጂውን) ለየብቻ በሠም ወይም በሌላ ማጣበቂያ በማሸግ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው አየርላይ ከዋለበት ቀን እስከ 10ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በmo ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04፡00 ላይታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳረሽ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ጨረታ የሚከፈትበት ቀን አመት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4፡30 ይከፈታል።
8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
10. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. እኩል ውጤት ያገኙ ተጫራቾች ተጨማሪ የማወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይደረጋል። ለሶስተኛ ጊዜ እኩል ከሆኑ በእጣ እንዲለዩ ይደረጋል ፡፡
12. የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በከፍል ሶስት እና ክፍል ስድስት በተጠቀሱት መሰረት ብቻ ይሆናል ።
13. ተጫራቾች ሁሉንም የመወዳደሪያ ሰነዶች ህጋዊ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞባቸውና የድርጅታቸውን ማህተም አርፎባቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
14. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀን እና ለተጨማሪ 28 ቀን የሚቆይ ይሆናል። የጽዳት አገልግሎት የአንድ ዓመት ጊዜ ጸንቶ የሚቆይ ዋጋ የሚሞላው እንደሆነ መታወቅ ይኖር በታል።
15. መስሪያቤታችን ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0112769862/0112732771 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
