በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ /ፋ/ጽ/ቤት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ /ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በመደበኛና በካፒታል በጀት ዓመት በሎት ከፋፍለን ያቀረብናቸው እቃዎች፤
1/ ሎት አንድ የእስቴሽነሪ ግዥ
2/ ሎት ሁለት የኤሌከትሮኒከስ እቃ ግዥ
3/ ሎት ሶስት የፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት-
1/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዘርፉ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተጨማሪም የእቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2/ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አስር ሺህ ) ብር ብቻ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በተናጠል በሎት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3/ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን ማስፈርና የድርጅታቸው ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
4/ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
5/ ማንኛውም ተጫራች ሰነዶቹንና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በፖስታ በማሸግ 1 ኦርጅናል ቴከኒካል እና 1 ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶከሜንት በጥንቃቄና በታሸገ ፖስታ በምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ላይ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
6/ ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ በምስራቅ መስቃን ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 4 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
7/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ /የሕዝብ በዓል/ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡
8/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ከፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
9/መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከታወቀ ውል ከገባ በኋላ ንብረቱ እስከ መሥሪያ ቤታችን ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-04-63-21-01-58
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን
በምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
