ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/07/18
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ
ሎት 1:(Office Equipment)
ሎት 2፡የመኪና ግዥ (Coaster electric midi- Bus)
ሎት 3- የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች (Office Fumiture & Fittings) ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.አ እና የእቃው ዝርዝር መግልጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም እቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንደትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶከመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ከፍል ብር 100.00 በመከፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡ 00-6:00 እንዲሁም ከሠዓት 7:00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 ለእያንዳንዱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች የመጫረቻ ዶከመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ያሸነፈ ተጫራች የእቃዎች ርከከብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ከፍል ስልክ ቁጥር 011-555 19 11
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
